Skip to main content

KUE

Geez for Amharic


ይህ ኮርስ ሁለት የመማር ማስተማር አካሄድን የተከተለ ይሆናል፡፡ የመጀመሪያው የትምህርቱ ንድፈ ሐሳባዊ ዳራ በመምህሩ ገለጻ የሚደረግበት ሲሆን፣ገለጻ የሚደረግባቸው

Enrollment in this course is by invitation only

ይህ ኮርስ ሁለት የመማር ማስተማር አካሄድን የተከተለ ይሆናል፡፡ የመጀመሪያው የትምህርቱ ንድፈ ሐሳባዊ ዳራ በመምህሩ ገለጻ የሚደረግበት ሲሆን፣ገለጻ የሚደረግባቸው ርእሶችም፡- የግዕዝ ቋንቋ ታሪካዊ ዳራ፣ በግዕዝ ቋንቋ የተጻፉ ሥነ ጽሑፋዊ ስራዎች ቅኝት፣ የግዕዝ ፊደሎች ዓይነትና አገልግሎት፣ የግዕዝ አዞችና ፊደላዊ ገለጻቸው፣ የግዕዝ ሥርዓተ ንባቦች፣ የግዕዝ ተውላጠ ስሞች ዓይነት (ምድብ ተውላጠ ስም፣ ድርብ ተውላጠ ስም፣ ተሳቢ ተውላጠ ስም፣ መጠይቅ ተውላጠ ስም፣ አመልካች ተውላጠ ስምና ተቀባይ ተውላጠ ስም)፣ በዝርዝር ገለጻ ይደረግባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የግዕዝ ስሞች ዓይነትና መገኛ ክፍላቸው፣ የግዕዝ መስተዓምሮች ምንነት እና አገልግሎት፣ የግዕዝ ተውላጠ ስሞች ዓይነት (ምድብ ተውላጠ ስም፣ ድርብ ተውላጠ ስም፣ ተሳቢ ተውላጠ ስም፣ መጠይቅ ተውላጠ ስም፣ አመልካች ተውላጠ ስምና ተቀባይ ተውላጠ ስም)፣ እና የተውላጠ ስሞች ሙያ፣ የግዕዝ ቅጽሎች ዓይነትና መገኛ ክፍላቸው፣ ግስ፣ የግስ አይነቶች እና የግስ አረባብ ስርዓቶች፣ አንቀፅ አጎላማሽ (ተውሳከ ግስ)፣ ደቂቅ አገባብ (መስተዋድድ)፣ ዐቢይ አገባብ፤ እንዲሁም የዓ.ነገር ምንነት እና አይነቶች  በዝርዝር የሚዳሰሱ ይሆናል፡፡